በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች:
አንድ ኦንላይን ሲገዛ ምን ያህል መጫን ይቻላል?
- አንድ ኦንላይን ሲገዛ ሦስት መጫን ይቻላል። ከአንድ በላይ ለመጫን እርዳታ ወደሚለው በመሄድ/በመግባት መጫን የሚለውን በማንበብ እንዴት ከአንድ በላይ ፒሲ ላይ መጫን እንደሚቻል በዝርዝር መረዳት ይቻላል።
የሶፍትዌር መጫኛ አክቲቬሽን ኪ ቢጠፋ ተጠቃሚ ምን ማድረግ አለበት?
- የሶፍትዌር መጫኛ አክቲቬሽን ኪ ከጠፋ የሶፍትዌሩ ተጠቃሚ ስትገዛ/ሲገዛ የተጠቀመችውን/የተጠቀመውን ኢሜል በመጠቀም ኢሜል በማድረግ ችግሮችን በመግለጽ እና መልክት በመላክ ነው። ኢሜሉ እንደደረሰን የሚያስፈልገውን ኢንፎርሜሽን በመላክ እንረዳለን።
ለምንድን ነው እንደ ስም፣ ኢሜል፣ እና፣ የሴክዪሪቲ ጥያቄዎች የምጠየቀው?
- እንደ ስም፣ ኢሜል፣ እና፣ የሴክዪሪቲ ጥያቄዎች የሚጠየቁት ተጠቃሚ ኢንፎርሜሽን ቢጠፋበት/ቢጠፋባት በድጋሚ መክፈል እንዳይኖርበት/እንዳይኖርባት ነው። ለምሳሌ ተጠቃሚ አዲስ ኮንፒውተር ገዝቶ/ገዝታ መጫን ቢቸገር/ብትቸገር መርዳት እንድንችል ነው።
ፊደል በኮንፒውተርን ለመጠቀም ኦንላይን መሆን አለብኝ?
- ፊደል በኮንፒውተርን ለመጠቀም ኦንላይን መሆን አያስፈልግም። ነገር ግን መጀመርያ ሳፍትዌሩን ኮንፒውተር ላይ ሲጫን ኦንላይን መሆን ያስፈልጋል።
ፊደል በኮንፒውተር ሶፍትዌሩን ለመጫን መመርያ አለ?
- ሶፍትዌሩን ፒሲ ላይ ለመጫን ዝርዝር መመርያ አለ። የሚቀጥለውን "ሶፍትዌሩን ፒሲ ላይ ለመጫን" የሚለውን ሊንክ ተጫኑ ዝርዝር መመሪያውን ለማየት ሶፍትዌሩን ፒሲ ላይ ለመጫን ።
ለትምህርት ቤቶች እና ለበጎ አድራጎቶች ቅናሽ አላችሁ?
- ለትምህርት ቤቶች እና ለበጎ አድራጎቶች ቅናሽ እናደርጋለን። ቅናሽ ለመጠየቅ የትምህርት ቤቱን ወይንም የበጎ አድራጎቱን ስም እና የቅናሽ ጠያቂ ግለሰቡን ግንኙነት (አስተማሪ, ዳይሬክተር, .....) ከትምህርት ቤቱን ወይንም ከበጎ አድራጎቱን ጋራ ላኩልን የቅናሽ ኩፖን መላክ እንድንችል።
ተጨማሪ ጥያቄዎች ስለ ፊደል በኮንፒውተር ካላችሁ መልክት ለመላክ አታመንቱ።